ይፋጃል ወገን የመታሀው ምስማር ባለ 12 ቁጥሩን ነው ብል የሚሻል ይመስላል። ለምን ቢባል በበቂ ሁኔታ እንደገለፅከው ናፖሊዮን ሁሌም ልክ ነው የሚሉ የዘመኑ Grande Armée ከሰማይ በታች መለስ ሁሌም ልክ ነው የሚሉበት ዘመን አብቅቶ ከእውነት ጋር መታረቅ መፈለጋቸው መዳኛ ጥግ እያፈላለጉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ጨው ለራስሽ ስትዪ ጠፍጪ አሊያም ድንጋይ ብለው ይወረውሩሻል እንደሚባለው ንስሀው ከሁሉ በፊት ለራስ ነው።
ብራሾ ይፋጃል
በበርካታ አገራት አንደ ሰንሻይን የመሳሰሉ ታላላቅ ሪል ስቴቶች ባላቸው ሰፊ አቅም የሀገራቸውን የመኖሪያቤት እጥረት እና የዋጋ ንረት ለመገደብ ሲሰሩ ይታያሉ ሰንሻይን ግን በዚህ ዜና እንደምንረዳው በዋንኛነት ትርፍን የማጋባስ ኣላማ ዋንኛው መሰረቱ በመሆኑ 400000000 አራት መቶ ሚሊዮን በሚፈጅ ወጭ የገነባውን 210 ሁለትመቶ አስር ቤቶች ለያንዳንዳቸው በአማካይ 2000000 ሁለት ሚሊዮን በፈጀ ወጪ ገንብቶ ከእጥፍ በላይ ትርፍ በሚያስገኝ መንገድ እስከ 4000000 አራት ሚሊዮን እና ከዚያም በላይ ሲቸበችባቸው እናያለን ይህም የሀገሪቱን የመኖሪያ ዋጋ ከማረጋጋት ይልቅ በይበልጥ ሲያባብሰው ይታያል። ለመሆኑ የዚህ አይነቱ አሰራር ማብቂያው መቼ ይሆን
የሚደንቀው የፍርድቤቱ ውሳኔ ሳይሆን የተከሳሾቹ ፍጹም መልአክት መሆናቸው ነው።በአገራችን ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አንደሚባለው ወያኔን መክሰስ አይቻልም ብሎ መደምደም የሚቀል ነበር።በአንድ ጉዳይ እንኩዋን ወያኔ ሲረታ የማይታየው እውነት ከወደ ትከሻቸው ትንንሽ ክንፍ ያበቀሉ ፃድቃን ሆነው ይሆን-እንደው እውነት የፍትህ ስርእት በእገሪቱ ካለ ለህሊናው ፍርድ የሚሰጥበት ጊዜ ይድርስ ይሆን-የሚያሳዝን ነው።ነገም ሌላ ቀን ነውና ይህ ሁሉ አሳዛኝ ሁኔታ አልፎ በህዝብ ላይ ይህንን በደልና ግፍ የሚጭኑ ሁሉ በሰፈሩበት ቁና የሚሰፈሩበት ጊዜ ይደርስ ይሆናል አስከዚያው ቅሎች ድንጋይ እየሰበሩ መግፋታቸው የግድ ሆኖአል።
ታጋይ መርጋ የዘነጉት ነገር ቢኖር የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ቀደምሲል የተፈራረሙት ከውጭ ጉዳይ ጋር እንጂ ከምርጫ ቦርድ ተብዬው ጋር አይደለም። ታዲያ በምን መንደርደሪያ ነው መርጋ ህብረቱን ለመተቸት የበቁት- በቅድሚያ የስምምነቱን መነሻ እና መዳረሻ አብረው በወያኔ ድርጅታዊ ስራ ውስጥ ተሳትፈውበታልና ዝርዝሩን ማወቃቸውን ለመግለፅ ከሆነ ይሄ ሊያስማማ ይችላል።ካልሆነ ግን አቀራረባቸው የሚያሳፍር ብቻ ሳይሆን የሚያስንቅም ጭምር ነው።ወያኔ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በቁጥጥሩ ውስጥ ማዋሉን በፉከራ በሚገልፅበት በአሁኑ ወቅት የሚታይ ጭስ ሁሉ ቢያስበረግገው የሚደንቅ አይደለም ለምን ቢሉ የአበሩን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም ነውና።
ጀግናው.--- ጀግንነት በምን እንደሚለካ ማወቁ በስሙ እንደ መፎከር የቀለለ አይደለም ። በርግጥ ዘመኑ በርካታ የሚያላግጠ- ጀግኖች ያየንበት በመሆኑ ያንተው ሳቅ አይደንቅም። ጀግናው- ወያኔ ከከፋው አምባገነናዊ ባህሬው በተጨማሪ ስር የሰደደ ይልኙታቢስ መሆኑን ጭምር የምትስተው አይመስለኝም ።ይልኙታ ሀገራዊ የሆነ መለያ ቅርሳችን የሆነው እንደ ኢትዮጵያዊ በአንድ ውቅት ከሰራነው ስህተት የምንማር መሆናችንን ስለሚያመሳክርልን ነበር።ሆኖም ወያኔ ግን ይህንን የመሰለ አገራዊ መገለጫ የሆነውን ይሉኝታ አልፈጠረበትምና ደጋግሞ ለሚሰራው ስህተትና ወንጀል መለስ ብሎ ለማሰብ የሚቻለው አይደለም።ለዚህም ነው ወያኔን ከርሞ ጥጃ ነው ማለት የሚቀለው።ጥላቻን፥ንቀትን፥ክህደትን እና ጭቃኔን መርሁ ላደረገ እንደወያኔ ካለ ሀይል በርግጥ ይሉኝታን መጠበቅ የዋህነት ነው። እናም ወያኔ ሐሰትን በድራማ ተውኔት እሽሞንሙኖ ባቀረበ ቁጥር የሚሞኝ የዋህ ዛሬ የሚገኝ አይመስለኝም።እናም ያለው አማራጭ ዛሬ አንድ እና አንድ ነው ይሀውም ወያኔ ከገባበት ማጥ በራሱ ሀይል መውጠት መቻል ብቻ።ያኔ አንተም ወንድሜ እውነተኛውን ሳቅ መሳቅ ይቻልሀል ብዬ አምናለው።
ቸር ሰንብት
ዶክተር አሸብር በምርጫ ሳይሆን በማሙያ መልክ ወያኔ እድሉን የከፈተላቸው ተወዳዳሪ ቢባሉ የሚቀል ይሆናል።ለምን ቢባል ወያኔ ያልፈለገውን ግለሰብ ለማስወገድ ግምገማ ሳያስፈልገው ስራውን እሳቸው የፈጸሙለት በመሆኑ።ግለሰቡ እንደ አንድ ተወዳዳሪ ይህ ነው የሚባል የመወዳዳሪያ አጀንዳ ሳይዙ እንደው በደመነፍሰ ያልወደዱትን ለማግለል ብቻመንቀሳቀሳቸውን የተከታተል ሁሉ የሚረዳው ቁምነገር ቢኖር በሁሉም መስክ ምርጫው ምን ያህል የዘቀጠ እና እንደ ግለሰብ የጠላኽውን ግለሰብ እንደ ፓርቲ ደግሞ ያልወደድከውን ፓርቲ የህዝብ ጠላት አድርጎ በማቅረብ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማቃራን በተለይ ወያኔ ሁነኛ ስራ በመስራት የተሳካለት መሆኑን የተገነዘብንበት ነው።ወያኔ ባለፉት19 አመታት ወስጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎ ለመምታት የቻለብትን የተሳካ ስራ የሰራበት ወቅት ቢኖር አሁን የምንገኝበት ጊዜ ነው ቢባል የሳተ እየደለም።ይህም በቀጥታ በድርጅቱና እንደ አሸብር በተዘዋዋሪ ያሰለፋቸው ሃይሎች ያገኙትን አምባገነናዊ እድል መመልከት ይቻላል።እናም ከዚህ የምንማረው አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን ማጥና በሕዝቡ ሉአላዊነት ላይ ያጠላውን አደጋ ነው።
ትንሽ ቀልድ ለአቶ መንበረ የምትመች ቅቅቅቅቅቅ
ሟችነፍሱ ሰማይ ቤት እንደደረሰ የሰማይ ቤት ዳኞች ገሃነም ወይም ገነት ለመግባት ሁለቱንም ስፍራዎች ጎብኝቶ መምረጥ እንዳለበት ይነግሩታል፡፡ በመርሐ-ግብሩ መሰረትም በመጀመሪያ ገሃነምን እንዲጎበኝ ይጋበዝና ገና ከበሩ ላይበመልካም አለባበስ የተሸቆጠቆጠው ሳጥናኤል በሞቀ ሰላምታ ተቀብሎት ወደ ውስጥ ይዞት ይገባል፡፡
ገሃነም ውስጥ የሟች የድሮ ወዳጆች ሁሉ ተሰብስበው እየጠጡ፣ ከረንቦላ እየተጫወቱ፣ በሙዚቃ እየጨፈሩ አስደሳች ጊዜ ሲያሳልፉ ተመለከተ፡፡ ከዚያም ወደ ገነት ተወሰደ፡፡ ገነት እንደገባ አንድም የድሮ ጓደኛውን ሊያገኝ አልቻለም:: ከዚያም በላይ ሲያስበው ያስመረረው ግን በገነት ያሉ ሰዎች ስራቸው ሁሉ ነጫጭ ለብሰው ማሸብሸብ፣ መጸለይና መስገድ ብቻ መሆኑ ነው ፡፡ ሟች ሁለቱንም ሁኔታዎች አመዛዝኖ ሲያበቃ ገሃነም ከወዳጆቹ ጋር ለመቀላቀል ወስኖ ፊርማውን አኖረ፡፡ በማግስቱ ወደገሃነም ሲወሰድ ግን የጠበቀው ነገር ሌላ ነበር፡፡ ሳጥናኤል በአስፈሪ እርቃኑ ቆሞ እህል-ውሃ የማያሰኝ ጅራፍ ይዞ እየዠለጠ ወደ ውስጥ አስገባው፡፡ ውስጥ የነበሩት ጓደኞቹም ግማሽ ሰውነታቸው በእሳት ተዘፍቆ ሲሰቃዩ ተመለከተ፡፡ ወዳንድ ጓደኛው ጠጋ አለና ትላንትና ያየሁት ሕይወት የት ሄደ? ብሎ ቢጠይቀው፡፡ አይ እሱማ የምርጫ ቅስቀሳ ነው ብሎት እርፍ አለ፡፡
ወንድም ፍቅሩ እንደው ከርሞ ጥጃ ብልህ ይሻል ይሆን--ስለአቶ ልደቱ የፖለቲካ ሞት መሞት ከዚህ የተሻለ ምን ማስረገጫ ያስፈልጋል፥በከተማም በገጠርም የሚገኝ ሕዝብ አንቅሮ ሲተፋው እያየህ-ይህ የህዝብ-ውሳኔ ልደቱ በተከታታይ በሕዝብ ላይ ለሰራው በደል የተሰጠው ምላሽ እኮ ነው።ልደቱ በሕዝቡ ውስጥ ያለውን ጥያቄ አሳንሶ የሶሰተኛ መንገድ ደቀ-መዝመርነት ሲያምረው አኮ ነው ሕዝብ በቃሀኝ ያለው።ወያኔ ከተያያዘው አረመኔዊው ተግባሩ ኢምንት ፈቅ ሳይል የሱ ከወዲህ ወዲያ መላጋት ምን ለመጨበጥ ሲባል ነበር--እናም የሕዝብ ጥያቄ ሆነው የቀጠሉትን በሱ መንሸራረት ማስቀረት የሚቻል ያለመሆኑን መረዳት ቢገባው የተሻለ ነበር። ልደቱ ዛሬ በመግለጫ ጋጋታ ሕዝብን እያራከሰ እና አያዋረደ መቀጠሉ ለፓለቲካ ሞት መሞቱ አይነተኛ መግለጫው እኮ ነው አሊያማ ሕዝቡ በአሁኑ ወቅት የሱን ዲስኩር የሚያዳምጥበት ትእግስቱ ማለቁን ከእርሱ በላይ ማን አውቆት--እናም ልደቱ አገራችን በፓለቲካው መስክ ካፈራቻቸውና በአሳፋሪ ተግባራቸው ህዝብ በታሪክ ሲያስታውሳቸው ከሚኖሩት ውስጥ ዋናውን ስፍራ የሚይዝ ነው። ስለዚህ አቶ ልደቱን አሁን የሚያስፈልጋቸው የፖለቲካ ነፍሳቸውን እግዜሃብሄር ይማረው ማለት ብቻ ነው። የሚማር ባይሆንም።
ሪፖርተር ለአቶ ልደቱ ያቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢ የሚባሉትን ነው። ነገርግን ከነዚህ ጥያቄዎች በተጨማሪ አቶ ልደቱ በተጨማሪ ቢመልሱት የሚገባው ጥያቄ ቢኖር፧ ወደ ቡግና ለምርጫ ከማቅናታቸው በፊት ወያኔ ከከተሞች አካባቢ ይልቅ በገጠር ወረዳዎች በሕዝቡ ላይ የሚያሳርፈውን ከፍተኛ አፈናና ጫና እንዳለና ይህንንም ቀደም ሲል በተደረጉ ምርጫዎች በሚገባ የሚያውቁት መሆኑን ከዚህም በተጨማሪ በተለይ የውጭ ታዛቢዎች በቅርብ በገጠር ወረዳዎች ተገኝተው ለመከታተል አለመቻላቸው፧እንዲሁም ሕዝቡ ብሶቱንና በደሉን የሚያስተጋባበት እድል በገጠሩ ከከተማው ይባስ የከፋ መሆኑን እየተረዱ ገጠሩን የመረጠ-ት ምን ያህል በከተማው ሕዝብ ተስፋ ቢቆርጠ- ነው የሚል ነበር
ለነገሩ አቶ ልደቱ የፖለቲካውን ሞት አልሞት ማለታቸው እንጂ ሕዝቡ በከተማም ይሁን በገጠሩ አንቅሮ ከተፋቸው ሰነበተ።
ወንድሜ ያሲን እውቀት ረከስ ይሉሀል ይሄ ነው ።