Abualexx

Abualexx

64p

11 comments posted · 14 followers · following 0

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ወይዘሪት ብር... · 0 replies · +1 points

አቶ ታምሩ ወ/አገኘሁ በ97 ምርጫ የቅንጅት አመራር አባላት ፓርላማ አንገባም ብለው አሻፈረኝ ሲሉ እንዲህ ብለው ምክር ለግሰውላቸው ነበር :: ".... በአገራችን ታሪክ ከፖለቲካ ተሳትፎ የተገለለ ወይም የወጣ ተመልሶ አያውቅም :: / ለምሳሌ : መኢሶን : ኦነግ : / ከወጣችሁ ህገ ወጥነታችሁ ታረጋግጣላችሁ እንጂ ሌላ ፋይዳ የለውም :: መታኮሻ ምሽጉ ያለው በተመረጣችሁበት ምክር ቤት ስለሆነ አስቡበት :: " ብለዋቸው ነበር :: አሁንም ወ/ሮ ብርቱካን " የ-PENNSYLVANIA አርበኞች " አንሸራርተው በመጣል እዛው እንዳያስቀሯቸውና በዛውም እንዳይመሽባቸው ቆም ብለው ማሰብ ይጠበቅባቸዋል ::

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የቀዳማዊ ኃይ... · 1 reply · +20 points

ፊውዳሎቹ መጀመርያ ግዮን ሆቴል በጨረታ አሸንፈው እንደገዙትና በ7 ቢልዮን ብር እንደገና አፍርሰው እንደሚሰሩት ተነገረን :: አሁን ደግሞ ንጉሱ ጭቁኑን የአገሬው ህዝብ በመበዝበዝ ያሰሩት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለልጅ ልጆቻቸው ተረከበ እየተባልን ነው :: በየትኛው መለኪያ ይሆን በሙስና የተገነባ ሆቴል ንጉሱ " የጉልበት ስራ " እየሰሩ ያፈሩት ንብረት ይመስል ለልጅ ልጆቻቸው የሚተርፈው ?? እንዲህ ከሆነ ለአሁኖቹ ባለስልጣኖቻችንም የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፉ " ሃሳብ አይግባቹ " እናንተ እንኳን ባትበሉት ለልጅ ልጆቻቹ ይተርፋል ማለት አይሆንም ??

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የዲቪ አመልካ... · 0 replies · -1 points

እውነትም ድንጋይ ራስ !! አርእስቱ ሌላ እሱ የሚዘባርቀው ሌላ :: እስኪ እዚህ ምን አመጣቸው ? እነ አባዱላ ገመዳ..... ዳባ በደሌ...... ኦህዴድ.... ከርቸሌ...... ምንትስየ... ዝባዝንኬ......???

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የመድረክ ተወ... · 1 reply · +6 points

Arbagnaw....! ያልገባህ ነገር ቢኖር በአሁኑ ግዜ ብቸኛው የትግል ምሽግ ያለው ፓርላማ ብቻ መሆኑ ነው :: ሰላማዊና አመጽ እያጣቀሱ መጓዝ ጊዜው አልፎበታልና ::

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - መድረክ በአገ... · 0 replies · +7 points

በ 97ቱ ምርጫ 10 ሚልዮን የሚጠጉ መራጭ ዜጎች : የጠዋት ብርድና የቀን ጸሃይ ተቋቁመው : እንደ አባባላቸውም......... የገዢው ፓርቲ እንግልት : በደልና ጥቃት ችለው በማለፍ : የሰጧቸውን ድምጽ እና አደራ መወጣት ያልቻሉ ጀግኖች : አሁንም በድጋሚ " ለስልጣን የታጨሁ ልዩ ሃይል ነኝ " የሚለው ልክፍታቸው በምርጫ ከጨዋታ ውጭ በሆኑበት ግዜም ማርሽ መቀየር አለመቻላቸው በጣም ይገርማል :: ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ብዙ ስሜታዊነታቸው የገዘፈ ሁኖ ለጎጂ ውሳኔ የሚያደርሱ ፈተናዎች ማለፍ የሚጠይቅ የሃገር መምራት ከባድ ሃላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ነን የሚሉ ምሁራኖች በዚያን ጊዜ በተወሰኑ የደህንነት ሰራተኞች ፈጸሙት የተባለው ማስፈራራትና ዛቻ ለዛውም ከምሽቱ የማያልፍ ተግባር ተገፍተው የሚልዮኖች ድምጽ አሽቀንጥረው የጣሉ ሰዎች አሁን ተመልሰው ኢህአዴግ ሃገራዊ በሆኑ አጀንዳዎች ሊደራደረን ይገባል ማለታቸው ፖለቲካዊ ቀመራቸው ምን ያህል የተዛባና የተንሻፈፈ መሆኑ በቂ ማስረጃ ነው :: በመጨረሻም እነዚህ ሰዎች መንግስታዊ ስልጣን ቢጨብጡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ለሚለው ግምት በጣም አስፈሪና ጨለማም ነው ::

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ወይዘሪት ብር... · 1 reply · +1 points

elyaad..... በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር " በኢትዮጲያውነትህ እራስህን መስለህ ኑር " ለሚለው አይዶሎጂ እናንተ ተቃዋሚ ነን የምትሉ ሰዎች ያላቹ አመለካከት በጣም የተንሻፈፈና የተዛባ ነው :: በየትኛው የፖለቲካ የትንተና ዘይቤ ይሆን ለዜጎች ራሳቸው በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ መፍቀድ የዘረኝነት ፖለቲካ የሚሆነው ? እንደገናም ኢትዮጲያ ውስጥ አንቀጽ 39 ቢኖርም ባይኖርም በጋራ መኖር የሚያስችል አመለካከትና ዴሞክራሲ ከሌለ ሰዎች ከስርአቱ መቀጠል አንችልም ማለታቸው የማይቀር ነው :: አንድነት ማምጣት የሚቻለው " ብትፈልጉም አትወጡም ብሎ " ህዝቦችን በመርገጥ ሳይሆን : ህዝቦች ከኢትዮጲያውነት ይበልጥ እንዲጠቀሙ በማድረግ የትልቅ ውጤት አካል የሚሆኑበት ስርአት ሲፈጠር ብቻ ነው :: በመጨረሻ ስለ ጨዋነት ከመመጻደቅክ በፊት መጀመርያ የጻፍከውን መልሰህ ቃኝና ምናልባት ባህሉ ካለህ ፓርቲ የሚያክል ነገር ከመውቀስህ በፊት እራስህን ትገስጽ ይሆናል ?

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ወይዘሪት ብር... · 3 replies · -1 points

ዝም ብለህ አታካራ ከምታበዛ " በኢትዮጲያውነትህ እራስህን መስለህ ኑር " ለሚለው ሃረግ ከዛ የህዝቦች መብት ለመርገጥ መጠቀምያ የነበረው አንድነት የሚባለው ሀረግ ሌላ በምትኩ ተቀባይነት ያለው ሃሳብ ካለህ አምጣ :: ግን.... ከዛ አንገታችን ተቆረጠ........... እግራችን ተገነጠለ......... የሚለው በጣም አሰልቺ ትንተና ውጭ !!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ወይዘሪት ብር... · 6 replies · -1 points

1000 ሺ አመት ሙሉ በአንድነት ስም " እኔን መስለህ ኑር " የሚለው አመለካከት በተግባር ተሞክሮ አገሪትዋን ወደ ማያባራ ጦርነት የከተታት ስለሆነ : አሁንም ሴትየዋ ይሄን ያረጀና ያበቃለት አመለካከት መልሳ ከምታመነዥክ : የ21ኛው ክ/ዘ የሆነውና ብቸኛው መፍትሔ " በኢትዮጲያውነትህ እራስህን መስለህ ኑር " የሚለውን አይዶሎጂ ቢመራትም በጸጋ ተቀብላ ካልተጓዘች አሁንም ሴትየዋ " ውሃ ቢወቀጥ እምቦጭ " ናት ማለት ነው

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ወይዘሪት ብር... · 2 replies · +7 points

የተፎካካሪህን አቅምና ብቃት ሳትገመግም በስሜት ብቻ የምትነዳ የብርቱካን አይነት ፖለቲከኛ ከሆንክ እራስህን ብቻ ሳይሆን በስሜት ደጋፊ የሆነውም ጭምር ይዘህ ገደል የሚገባበት አጋጣሚ ስላለ " የዜሮ ድምር " ፖለቲካ አራማጆች የሆናቹ በሙሉ ከሴትየዋ ትምህርት ትቀስሙ ዘንድ በትህትና ትጠየቃላቹ ::

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - መድረክ የወ/... · 3 replies · +2 points

Antiterrorist , ሴትየዋና የቀድሞው የቅንጅት ኣመራር ህገ-መንግስቱና ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በአመፅ ለመገርሰስ በመሞከራቸው ፣ በዚህ ኣጋጣሚም ለጠፋው ሂወትና ንብረት ተጠያቂ መሆናቸው የፌደራል ኣቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ መሰረት ፣ ጥፋተኞች ሁነው በመገኘታቸው የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ሞትና የእድሜ ልክ እስራት ከፈረደባቸው በሃላ ነበር መፀፀታቸውን በመግለፅ ህዝብና መንግስትም ይህን ተገንዝቦ ይቅር አንዲላቸው ፤ እነሱም ህገ-መንግስቱና ህገ-መንግስታዊ ስርኣቱን ማክበር ብቻ ሳይሆን አንደሚያስከብሩ ቃል በመግባት ስማቸውና ፊርማቸው በማኖር በግልፅ ጠይቀው ካበቁ በሃላ መንግስትም ይቅር መባባሉ ብሄራዊ ጥቅም አንዳለው በመገንዘብ የይቅርታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ይቅርታ አንዲደረግላቸውና ለወደፊት ተመሳሳይ ወንጀል የፈፀሙ አንደሆነ ግን ፍርዱ አንደሚፀና በማስገንዘብ ነበር ከእስር የለቀቃቸው።
ከዚህ ሁሉ በሃላ ነበር ሴትየዋ አኔ በድርድርና በሽምግልና አንጂ ይቅርታ ኣልጠየኩም ብላ መግለጫ የሰጠችው ። ከሆነም በሃላ በስሜት ወይም በሞቅታ አንዳይሆን የተናገረችው በማለት ኣገርቤት ከተመለሰች በሃላ መንግስት በተደጋጋሚ ማስተባበያ አንድትሰጥና የተናገረችውም አንድታስተካክል ስትጠየቅ አምቢ ኣልች
ስለዚህ ከመጀመርያውም በተለይ ሴትየዋ በተሳሳተና በተጭበረበረ ይቅርታ ነበር የጠየቀችውና ፍርዱ አንዲፀናባት መወሰኑ ትክክለኛ ከመሆኑም በላይ ለመሰሎችዋ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ባይ ነኝ ። በሃገር ውስጥና በውጭ የሚገኙት የዜሮ ድምር ፖለቲካ ኣራማጆች የሴትየዋ ጉዳይ ለፖለቲካ መሳርያ ለመጠቀም መሞከር ግን ባጭሩ ይቺ ሴትዬ ከእስር ወጣች ማለት ደርግ ከመቃብሩ መነሳት አንደሆነ ይቁጠሩት ።